አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ማይክሮሶፍት በዊንዶውስ 10 የመተግበሪያ ስርዓት አጋጥሞ የነበረውን ችግር መፍታቱን አስታወቀ።
በርካታ ተጠቃሚዎች መተግበሪያው ከትናንት ጀምሮ መስራት ማቆሙን ገልጸው ነበር።
ተጠቃሚዎች እንደገለጹት በዴስክቶፕ መረጃ መፈለጊያ ትዕዛዝ ሲጠይቁ የሚፈልጉትን ነገር ከማግኘት ይልቅ ባዶ ሳጥን ያገኙ ነበር።
ኩባንያውም የተጠቃሚዎችን ሪፖርት ካገኘ ከሰዓታት በኋላ የብዙ ተጠቃሚዎችን ችግር መቅረፍ መቻሉን አስታውቋል።
ይሁን እንጅ አሁንም አንዳንድ ተጠቃሚዎች ኮምፒተሮቻቸውን እንደገና ማስጀመር ወይም ሪስታርት ማድረግ ሊያስፈልጋቸው ይችላል ብሏል።
ኩባንያው ምን ያህል ሰዎች ይህ ችግር እንዳጋጠማቸው ግን ያለው ነገር የለም፡፡
ዊንዶውስ 10 መተግበሪያ ሥርዓት በዓለም ዙሪያ 800 ሚሊየን የሚሆኑ ተጠቃሚዎች አሉት።
ምንጭ፦ ቢቢሲ