Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የምክር ቤቱ አባላት የህገ መንግሥት የበላይነት እንዲረጋገጥና ህብረ ብሔራዊነትን ለማጠናከር ሊሰሩ ይገባል

አዲስ አበባ፣ መሰከረም 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ)የምክር ቤቱ አባላት የህገ መንግሥት የበላይነት እንዲረጋገጥና ህብረ ብሔራዊነትን ለማጠናከር ሊሰሩ ይገባል ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለስድስተኛው የፖርላማ ዘመን ለምክር ቤቱ አባላት ስልጠና እየሰጠ ነው።

ስልጠናው በምክር ቤቱ ህገመንግስታዊ ስልጣንና ተግባራት እንዲሁም የአሰራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል።

በዚህ ወቅት የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ አደም ፋራህ እንዳሉት ÷የምክር ቤቱ አባላት የህገ መንግስት የበላይነት ለማረጋገጥ ሊሰሩ ይገባል።

አባላቱ በአገሪቱ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ሊሰሩ እንደሚገባም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ የተከናወኑ መልካም ተግባራትን ማስቀጠል እና የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚጠበቅባቸው አፈ ጉባኤው አብራርተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version