Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር እየተሰራ ነው -የደባርቅ ከተማ ከንቲባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም እና በአስተማማኝ ሠላም ውስጥ ሆነው ወደ መኖሪያ ቄያቸው እንዲመለሱ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን የደባርቅ ከተማ ከንቲባ ገለጹ።
ከአሸባሪው እና ከዘራፊው የህውሀት ቡድን ጥቃት ለመዳን ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ተፈናቃዮች በደባርቅ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተጠልለው እንደሚገኙ የደባርቅ ከተማ ከንቲባ አቶ ሠለሞን ተዘራ ተናግረዋል።
አሸባሪው የህውሀት ቡድን በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ተመቶ ከመበታተኑ በፊት በዛሪማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ጥቃት አድርሷል ብለዋል።
በዛሪማ እና በሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች በዘላቂነት ለማቋቋም እና በአስተማማኝ ሠላም ውስጥ ሆነው ወደ መኖሪያ ቀያቸው እንዲመለሱ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሀገራችን ጠላት የሆነውን አሸባሪው የህውሀት ቡድን ሙሉ በሙሉ እስኪደመሰስ ድረስ እንደ ከዚህ ቀደሙ በደባርቅ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን ይቆማሉ ማለታቸዉን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
692
People Reached
218
Engagements
Boost Post
202
3 Comments
8 Shares
Like
Comment
Share
Exit mobile version