Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደቡብ ክልል ምክር ቤት 25 የቢሮ አደረጃጀቶችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ስድስተኛ ዙር መስራች ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የደቡብ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የክልሉን መንግስት የአስፈጻሚ አካላትአደረጃጀት፣ስልጣንና ተግባር መወሰኛ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።
የመንግስት መስሪያ ቤቶች መዋቅር ጥናት አዋጁ በሀገሪቱም ሆነ በክልሉ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ፣ውጤታማ፣ዘላቂና ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችልና የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል እንደሆነ በአዋጁ ላይ ተቀምጧል።
በዚህ አዋጅ መሰረትም የደቡብ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ስር 25 ቢሮዎች የተዋቀሩ ሲሆን እነዚህ ቢሮዎችም የሚከተሉት ናቸው።
1. የሰላምና ጸጥታ ቢሮ
2. የፋይናንስ ቢሮ
3. ጠቅላይ አቃቤ ህግ
4. የግብርና ቢሮ
5. የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
6. የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
7. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
8. የውሃ፣ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ
9. የትምህርት ቢሮ
10. የጤና ቢሮ
11. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ
12. የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ
13. ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ
14. የገቢዎች ቢሮ
15. የባህልና ቱሪዝም ቢሮ
16. የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
17. የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
18. የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
19. የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
20. የፕላንና ልማት ቢሮ
21. የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
22. የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ
23. የደንና አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ
24. የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ
25. የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ቢሮ ናቸው።
ከነዚህ መዋቅሮች ውስጥ፣
23. የደንና አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ
25. የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ቢሮ
20. የፕላንና ልማት ቢሮ
14. የገቢዎች ቢሮ
21. የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ፣
በአዲስ መልክ የተቋቋሙ ወይም ስልጣንና ተግባራቸው ከፍ ያለ ወይም ሰፊ መዋቅር እንዲኖራቸው የተደረጉ ናቸው።
ራሱን የቻለ መዋቅር የነበረው የእንስሳትና አሳ ሀብት ቢሮ ደግሞ ከነሙሉ ተግባራቱ ወደ ግብርና ቢሮ እንዲካተት መደረጉን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version