አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የተከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በአል ካለፉት አመታት አንፃር በደማቅ ስነ-ስርአት መከናወኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
ከንቲባዋ በአሉ በሰላም መጠናቀቁን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።
ከ150 አመት በኋላ በአዲስ አበባ እየተከበረ የሚገኘው የኢሬቻ በአል ባለፉት 3 አመታት ጀምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደመቀ መምጣቱንም ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ከ3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአሉን በደማቅ ስነ-ስርአት ማክበራቸውንም ነው ከንቲባዋ የገለፁት። በመዲናዋ በአሉ ሳምንቱን ሙሉ በተለያዩ ስነ-ስርአቶች ሲከበር እንደነበርም አንስተዋል። የአዲስ አበባ ህዝብ የኦሮሞ ወገኖቹን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ያሳየው ድጋፍ እና ፍቅር በመልካም ምሳሌነቱ የሚነገርለት ነው ብለዋል ወይዘሮ አዳነች አቤቤ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!