የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የመንግስት ምስረታ ጉባዔ ማካሄድ ጀመረ

By Tibebu Kebede

October 02, 2021

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር መስራች ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

አዲሱ ምክር ቤት በ5 አጀንዳዎች ላይ በመምከር የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ተጠባቂ ናቸው። በዚህም መሠረት፡-

1/ የአዲሱን ምክር ቤት ዋና እና ምክትል አፈ ጉባኤዎችን መሰየም

2/ የክልሉን መንግስት ርዕሰ መስተዳደር መሰየም

3/ የክልሉን አሰፈፃሚ ተቋማት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣ የመዋቅር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን ማድመጥ እና ውሳኔ ማሳለፍ

4/ የክልሉን መንግስት የካቢኔ አባላት ሹመት እና

5/ የፌዴረሽን ምክር ቤት አባላትን የመወከል አጀንዳዎች አዲሱ ምክር ቤት በመጀመሪያ መስራች ጉባኤው የሚመለከታቸው ጉዳዮች ናቸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ምንጭ:- ኢቢሲ