Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቅድመ – ብቅለት በቆሎ ጸረ አረም ኬሚካል መጠቀማችን ውጤታማ አድርጎናል – አርሶ አደሮች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመጀመሪያ ጊዜ የቅድመ – ብቅለት በቆሎ ጸረ – አረም ኬሚካል መጠቀማቸው ውጤታማ እንዳደረጋቸው በደቡብ ጎንደር ዞን የደራ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ባለሙያዎች በደራ ወረዳ በሚገኘው የጉና በቆሎ ምርጥ ዘር ብዜት ማሳ የመስክ ምልከታ አድርገዋል።
በምልከታውም በወረዳው ለበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜት የተዘራው ማሳ ጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤርሚያስ አባተ ተናግረዋል።
ለዚህም አርሶ አደሮች የተጠቀሙት “ሹርስታርት ኤስ ኢ” የተሰኘው የቅድመ -ብቅለት በቆሎ ጸረ -አረም ኬሚካል ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ነው የገለጹት።
የቅድመ – ብቅለት ቦቆሎ ፀረ-አረም ተጠቃሚ አርሶ አደሮች በበኩላቸው ፥ ፀረ አረሙ ለበቆሎ ምርጥ ዘር የዘሩት ማሳ ውጤታማ እንዲሆን ማስቻሉን አንስተዋል።
በቆሎ ከተዘራ በኋላ የሚወጣውን አረም ለመንቀል ብዙ የሰው ኃይልና ጉልበት ያባክኑ እንደነበር የገለጹት አርሶ አደሮቹ፥የቅድመ ብቅለት ቦቆሎ ፀረ አረም መጠቀማችው ይህንን ችግር እንደቀረፈላቸው ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም ፀረ – አረሙ የተዘራው በቆሎ ማሳ ላይ ምንም አይነት አረም እንዳይበቅል የሚያደርግ በመሆኑ የበቆሎው ምርታማነት ይጨምራል ነው ያሉት።
በወረዳው ለመጀመሪያ ጊዜ የቅድመ ብቅለት በቆሎ ጸረ – አረም በመጠቀም 522 ሄክታር መሬት ላይ የበቆሉ ዘር ብዜት መከናወኑም ነው የተገለፀው።
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version