አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ በአለምአቀፍ ንግድ ላይ ፈታኝ የሆነውን የኮንቴይነር አቅርቦት ችግር ለመፍታት አዲስ ግዥ መፈፀሙን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።
አሁን ያለውን የኮንቴይነር አቅርቦት ችግር ለመፍታት ግዢ የተፈጸመባቸው 106 ኮንቴይነሮች የገቢ ጭነቶች ይዘው በባቡር ሞጆ ወደብና ተርሚናል መድረሳቸውን የድርጅቱ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸብር ኖታ ለኢቲቪ ተናግረዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ባጋጠመው ከፍተኛ የኮንቴይነር እጥረትና የመርከብ ቦታ ጥበት ምክንያት የደንበኞች ጭነቶች በወቅቱ ለማጓጓዝ ተግዳሮት ገጥሞ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
በዚህም ድርጅቱ አዳዲስ ኮንቴይነሮችን በመግዛት ያጋጠመውን ወቅታዊ ችግር እየፈታ ይገኛል ነው
ብለዋል።
በተጨማሪም ድርጅቱ የሎጅስቲክስ አቅሙን ለመገንባትና የወጪ ገቢ ንግዱን ለማቀላጠፍ÷ተጨማሪ 5ሺህ ኮንቴይነሮችን ግዢ ፈጽሟል ብለዋል አቶ አሸብር።
የተገዙት ሁሉም ኮንቴይነሮች ጭነቶችን ከቻይና ይዘው ጅቡቲ የደረሱ ሲሆን÷ በቀጣይ ቀናት በተመሳሳይ ወደ ሞጆ ወደብና ተርሚናል የሚመጡ ይሆናል ብለዋል።
ድርጅቱ የሎጅስቲክስ አቅሙን ለመገንባትና የወጪ ገቢ ንግዱን ለማቀላጠፍ በቀጣይም ተጨማሪ ሁለት ግዙፍ መርከቦችንእና 240 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ግዥ ለማከናዎን በሂደት ላይ መሆኑ ኃላፊው ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!