የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር መስራች ጉባኤ በነገው እለት ይካሄዳል

By Feven Bishaw

October 01, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በነገው እለት 6ኛው ዙር የደቡብ ብሄሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ይካሄዳል።

በጉባኤው የአዲሱን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች፣ ርዕሰ መስተዳደር እና የክልሉን መንግስት የካቢኔ አባላት ይሰየማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡