አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አዲሱን አርማና የሰራዊቱን የደንብ ልብስ አስተዋወቀ፡፡
ኮሚሽኑ የአባላቱን አዲሱን የደንብ ልብስ በክልሉ ፖሊስ ማርች ባንድ ታጅቦ በአሶሳ ከተማ በመዘዋወር ለህብረተሰቡ አስተዋውቋል፡፡
የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አቢይ ጀጎራ፥ የኮሚሽኑ አበላት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተዘጋጀውን አዲሱን ደንብ ልብስ በመልበስ ሀገሪቱንና ህዝቡን እንዲሁም ታራሚዎችን በማረምና በማነጽ ተልኮአቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም በአሶሳ ዞን ማረሚያ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል የንጹህ መጠጥ ውኃ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
የክልሉ ሠላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ፣ በዞኑ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚሰጥ የንጹህ መጠጥ ውኃ ግንባታና መስመር ዝርጋታ የውኃ አቅርቦት በሲኤም ኤፍ አይ(CMF I) ተሠርቶ ለአገልግሎት መብቃቱን ገልጸው፣ ድርጅቱ ለበረከተው አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አባላት በበኩላቸው፥ አዲሱ አርማና የደንብ ልብስ ሃገራዊ ለውጡን ተከትሎ ኮሚሽኑ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱ እንዳስደሰታቸው ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share