አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከአለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር የአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሚል አሌአዋዲህን ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው በዋናነት በኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ባለው ወቅታዊና ቀጣይ ዕቅዶችን ለማሳካት እንዲሁም የተጀመሩ ታላላቅ ስኬቶች እንዲቀጥሉ ከአለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ጋር በመተባበር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡