Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከአለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር የአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ም/ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከአለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር የአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሚል አሌአዋዲህን ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው በዋናነት በኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ባለው ወቅታዊና ቀጣይ ዕቅዶችን ለማሳካት እንዲሁም የተጀመሩ ታላላቅ ስኬቶች እንዲቀጥሉ ከአለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ጋር በመተባበር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ሚኒስትሯም የአለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ባሳየዉ ቁርጠኝነት መደሰታቸውን መግለፃቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

Exit mobile version