Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከሰላም ማስከበር በተጨማሪ አርሶ አደሩ ምርታማነትን ለማሳደግ ያሳየው ተነሳሽነት ይደነቃል- የምድር ሃይል ዋና አዛዥ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊት የምድር ሃይል ዋና አዛዥና የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ በፓዊ ወረዳ የአርሶ አደሩን ማሳ ጎብኝተዋል።
በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ በዞኑ ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር ሳይበግራቸው በመደበኛው የግብርና ስራ ተሰማርተው የሚገኙ አርሶ አደሮች የልማት ብቻ ሳይሆን የሰላም አምባሳደሮች ናቸው ብለዋል፡፡
ሰላምን ለማስከበር በቅንጅት እንድምተሰሩት ሁሉ÷ የግብርና ስራዎችን በጋራ በማልማት የኢኮኖሚ አቅማችሁን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ይገባልም ነው ያሉት፡፡
የኢትዮጵያን ህልውና ለመታደግ እየተደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ የወረዳው ህዝብ ሰራዊቱን ከመደገፍ ባለፈ ወጣቱ ሰራዊቱን በመቀላቀል አሻራውን ማሳረፍ እንዳለበትም ጄኔራሉ ተናግረዋል፡፡
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በበኩላቸው÷ ከመደበኛ የግብርና ስራዎች በተጨማሪ አካባቢው ለመስኖ ስራ ምቹ በመሆኑ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር አርሶ አደሮች በዓመት ሁለት ጊዜ የሚያመርቱበት ሁኔታ እንደሚመቻች ጠቁመዋል፡፡
በወረዳው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሀገር የማዳን ዘመቻን በሁሉም መስክ ተሳታፊ እንዲሆኑ ከማድረግ በተጨማሪ የዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን የፓዊ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ አሰፋ ተናግረዋል፡፡
በወረዳው በተያዘው የምርት ዘመን ከ24ሺ 778ሄክታር በላይ መሬት በሰብል መሸፈኑን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version