Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ማይክ ፖምፒዮ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ማይክ ፖምፒዮ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።

ከየካቲት 9 እስከ 11 ቀን 2012 ድረስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አስታውቋል።

በቆይታቸውም ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም ወቅት በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሪፎርም መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ ብሏል መስሪያ ቤቱ።

በተጨማሪም በቀጠናዊ ጉዳችዮች ላይ ሀገራቱ ያላቸውን የጋራ ጥረትን ይመለከታሉም ብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በሴኔጋል እና አንጎላም ጉብኝት ያደርጋሉ።

Exit mobile version