አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑ አሸባሪ የህወሓት ቡዱን እያደረገው ያለ የጦር ቅስቀሳ ለትግራይ ህዝብ ዳግም ወደ ባሰ ችግር የሚዳርግ ነው ሲሉ የትግራይ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ትዴፓ) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉብርሃን ሃይለ ተናግረዋል፡፡
አቶ ሙሉብርሃን ሃይለ የአሸባሪው ህወሓት ቡድን የጦር መሪዎች ሰሞኑን በትግራይ ቴሌቪዥን የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሃላፊነት የጎደለው እንደሆነና የትግራይን ህዝብ ዳግም ወደ ከፋ ችግርና መከራ የሚዳርግ ነው፡፡
አሸባሪው ቡድን ያጋጠመው ችግር በውይይት ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ በጉልበት እፈተዋለሁ ማለቱ የትግራይን ህዝብ ዳግም ወደ ከፋ ችግር በመክተት ቡድኑ የራሱን ስልጣን ለማጠናከርና ከዚህ በፊት ከፈፀመው ወንጀል ከተጠያቂነት ለማምለጥ ማሳቡን ማሳያ ነው ብለዋል።
የትግራይ ህዝብ አሁን ከገባበት ችግር እንዲወጣ ግዜው የሚጠይቀውን ዘመናዊ ፖለቲከኛ ያስፈልገዋል ያሉት አቶ ሙሉብርሃን፥ የፖለቲካ ኪሳራ ያደረሰው አሸባሪው ፓርቲ ህወሓት ከዚህ በኋል አስተሳሰቡ የቀነጨረ በመሆኑ አዲስ ሃሳብ ሊፈጥር አይችልም ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!