አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን በ6 የምርጫ ክልሎች ድምፅ እየተሰጠ ይገኛል።
በዞኑ ምርጫው ባልተካሄደባቸው 6 የምርጫ ክልሎች 467 የምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ እየተሰጠ ይገኛል ።
ከ6ቱ የምርጫ ክልሎች አንዱ በሆነው ኪንዶ ኮይሻ ምርጫ ክልል 2 ጋሌ ሀ የምርጫ ጣቢያ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ድምፅ ሰጥተዋል።
በማስተዋል አሰፋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!