Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ ነው – ሀረሪ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነስሪ ዘከራያ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ምርጫው በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ አስፈላጊው የፀጥታ ሃይል መመደቡን አስታውቀዋል።
እስከአሁን ያለው የምርጫ ሂደት ካለምንም የፀጥታ እንከን እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ፥ ህብረተሰቡ በተቀረው ሰዓት ምርጫውን እንዲያከናውን ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምርጫው በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ፥ ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ እየሰራ ነው ብለዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version