የሀገር ውስጥ ዜና

በሐረር ከተማ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በይፋ ተጀመረ

By Meseret Awoke

September 30, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረር ከተማ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ከጥዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በይፋ ተጀምሯል፡፡

መራጩ ህብረተሰብም በተዘጋጁ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ይወክለኛል ለሚለው ድምጹን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ኢዜአ ምልከታ ባደረገባቸው የምርጫ ጣቢያዎችም የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱም ፍጹም ሠላማዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ነው።

በሐረሪ ክልል በሚገኙ 36 ቀበሌዎች 229 የምርጫ ጣቢያዎች አሉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!