የሀገር ውስጥ ዜና

በቤንች ሸኮ ዞን የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔና ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት ተጀመረ

By Tibebu Kebede

September 30, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ህዝበ ውሳኔና ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት በቤንች ሸኮ ዞን ተጀምሯል።

በቤንች ሸኮ ዞን በሶስት የምርጫ ክልሎች በሚገኙ 309 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የሚሰጥ ሲሆን÷ 127 ሺህ 126 የዞኑ ነዋሪዎች ድምፅ ለመስጠት ካርድ ወስደዋል።

ለሕዝበ ውሳኔው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ ለምርጫ ጣቢያዎች መድረሳቸው ታውቋል።

በዞኑ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ መስጠት መጀመሩን በሚዛን አማን ከተማ ተዘዋውረን ባየናቸው ምርጫ ጣቢያዎች መታዘብ ችለናል ሲል የዘገበውደሬቴድ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!