Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሀረሪ ክልል ነገ ለሚካሄደው ምርጫ ዝግጅት ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ነገ ለሚካሄደው ስድስተኛው ምርጫ በየምርጫ ጣቢያዎቹ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የየምርጫ ጣቢያዎቹ አስተባባሪዎች ገለጹ፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅኝት ባደረገባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ነገ ለሚደረገው የድምፅ አሰጣጥ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን ተመልክቷል።
አንዳንድ የምርጫ ጣቢያ አስፈፃሚዎች በሰጡት አስተያየት÷ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ማድረጋቸውንና ጣቢያዎቹም ለምርጫው ዝግጁ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
በተለይም ወጣቶች ምርጫ ጣቢያዎችን በማስዋብና ለምርጫው የተስተካከሉ እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውንም ነው የገለጹት፡፡
ነገ ለሚካሄደው ምርጫ በሀረሪ ክልል ሁለት የምርጫ ክልሎች በገጠርና በከተማ በሚገኙ 36 ቀበሌዎች በተቋቋሙ 229 የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጡ ይካሄዳል።
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version