Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አብን በማይጠብሪ ግንባር በህወሓት ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሰሜን ጎንደር ዞን ማይጠብሪ ግንባር በህወሓት ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የአይነት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የአብን አመራሮች ግንባር ድረስ በመገኘት ለሰሜን ጎንደር አስተዳደር ዞን የሎጀስቲክ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ወገኔ አማረ እና ለደባርቅ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰለሞን ተዘራ አስረክበዋል።
የተደረገው የአይነት ድጋፍም የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣ ብርድ ልብስ፣ ሩዝ ፣ ማካሮኒ እና ፓስታ መሆኑ ተገልጿል።
ፓርቲው በሁሉም ግንባሮች በሽብር ቡድኑ ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን አመራሮች ተናግረዋል።
በቀጣይም ፓርቲው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ከመንግስት እና ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ነው ያሉት።
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version