አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኤልዲፒ የአመራር ውድድርን አሸንፈው ቀጣዩ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ተዘጋጅተዋል።
የጃፓኑ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ የገዢው ፓርቲ የአመራር ውድድር ምርጫን በማሸነፋቸው
የአገሪቱ ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደርጋቸዋል፡፡
ኪሺዳ ቀደም ሲል የመከላከያ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትን ተፎካካሪያቸውን ታሮ ኮኖን በ257 ድምጽ አሸንፈው ለዚህ መብቃታቸውን ነው አልጀዜራ የዘገበው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!