Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተቋማት የመንግስት አገልጎሎቶችን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማቅረብ የሚያስችላቸውን ብሔራዊ ዳታ ማዕከል እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ አግባብ ለማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች በዘርፉ እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይ ሲ ቲ ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኢንጅነር አብዮት ሲናሞ ገለጹ፡፡
እስከዛሬ የለሙ አገልግሎቶችን በማስፋትና አዳዲስ ዘዴዎችን በመጨመር የመዋቅር ለውጦችን በቀላሉ ለማስተናገድ እንዲቻል ከ400 በላይ የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶች መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡
የተዘጋጁት አገልግሎቶች ከ40 በላይ የመንግስት ተቋማትን የአሰራር ሂደት ለውጦችን በቀላሉ በማካተት ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችል ቴክኖሎጂ ታግዘው ለመተግበር የተዘጋጁ ናቸውተብሏል፡፡
የለሙት የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶች በሚታጠፉና አዲስ በሚደራጁ የመንግስት ተቋማት የነበሩ የአሰራር ሂደቶችን በፍጥነት በማቀናጀት አገልግሎቶቻቸውን ለማስቀጠል የሚያስችሉና ወጭ ቆጣቢ መሆናውንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አገልግሎቶቹ በሚያስፈልጋቸው የባንድዊድዝ መጠን የተደገፉ እንዲሆኑ የወረዳ ኔት የባንድዊድዝ መጠንን በ 10 እጥፍ ከፍ በማድረግ ከ 2 ጌጋ ባይት ወደ 20 ጌጋባይት ማሳደግ ተችሏል::
ዘርፉ መስከረም 24/2014 የሚመሰረተው አዲሱ መንግስት በሚያቋቁማቸውና በሚያደራጃቸው ተቋማት የማህበረሰብ አገልግሎቶች በፍጥነት እና በጥራት ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ አገልግሎቶችን በሚፈለገው የ አይ ሲ ቲ መሰረተ ልማት እና ሲስተሞች ለመደገፍ አስተማማኝ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡
ዶክተር አብዮት በቀጣይ የሚደራጁ አዲስም ሆኑ ነባር ተቋማት ለመሰረተ ልማት ዝርጋታም ሆነ ለመሰል ሲስተምች ልማት ምንም ዓይነት ተጨማሪ ሀብት ወጪ ሳያደርጉ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር የሚገኘውን የብሔራዊ ዳታ ማዕከል መሰረተ ልማት እንዲጠቀሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version