አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በአዲስ መልክ የተቋቋመውን የከተማ አስተዳደሩን የአስፈጻሚ አካላት የአሰራር ማሻሻያ መዋቅር አፀደቀ።
የአሰራር ማሻሻያ መዋቅሩ በ126 ድጋፍ፣ በአንድ ተቋሞ እንዲሁም በአንድ ድምፀ ተአቅቦ ነው የፀደቀው።
አዲሱ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት በአስፈጻሚ አካላት የአሰራር ማሻሻያ መዋቅር ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ አጽድቆታል።
መዋቅሩ የተለያዩ መስሪያ ቤቶችን በአዲስ መልክ በማደራጀት እስከ ቢሮ ደረጃ እንዲዋቀሩ የሚፈቅድ መሆኑ ተመላክቷል።