Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሲዳማ ክልል ሰዉ ሃበት ልማት ቢሮ በ2013 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ላላቸው መዋቅሮች እዉቅና ሰጠ

አዲስ አበባ፣መሰከረም18፣2014 (ኤፍ ቢሲ)የሲዳማ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የተሻለ አፈፃፀም ላላቸው መዋቅሮች እና ግንባር ቀደም ፈፃሚዎች ዕውቅና የመስጠት ስነ-ስርዓት ተካሄደ።

በመርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ፣የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀገረፅዮን አበበ ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሁሉም ከተሞች እና ወረዳዎች አስተዳዳሪዎችና የፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

አቶ ደስታ ሌዳሞ በመድረኩ÷ ለህዝቡ የሚሰጠው አገልግሎት ህዝቡን ማስደስት በሚችል መልኩ መከናዉን እንዳለበት አሳስበው የአመራርነት ሰጪነት ድርሻን በማዘመን ብቁ እና በስነ- ምግባሩ የተመሰገነ ፐብሊክ ሰርቫንት መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀገረፅዮን አበበ÷ የሲዳማ ክልል በብዙ ትግል ክልል ከሆነ ማግስት አግባብነት ባለው እና በስርዓት የክልል ማዕከል መስሪያ ቤቶችን በሰው ሃይል ለማደራጀት እና ለመሙላት በማሰብ በአዋጅ በፈረሰው የሲዳማ ዞን ሰራተኞችን በጊዚያዊ ምደባ ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ማንሳታቸውን ከሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version