Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የምርጫውን ሰላማዊነት ለማረጋገጥ በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ተጨባጭ ስራ ተገብቷል-አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ የሚካሄደው ምርጫ ሰላማዊ ፣ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በክልሉ ከሚገኙ የተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፥እንደተናገሩት በክልሉ የሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፣ ዲሞክራሲያዊ ፣ ተአማኒ እንዲሁም በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ የህዝቡ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የግል እጩ ተመራጮች ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች እና የመንግስት ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል።
የክልሉ መንግስትም ምርጫው የተሳካ እንዲሆንና ዜጎች ያለ አንዳች ስጋት ወጥተው የሚፈልጉትን ፓርቲ እንዲመርጡ ከማስቻል አንፃርም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተለይም ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ሁሉንም የማህበረሰብ አባላት በማቀናጀት ፣ የምርጫውን ሰላማዊነት ለማረጋገጥ በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ተጨባጭ ስራ ተገብቷል ብለዋል።
በዚህም በተለይ የክልል እና የፌደራል የጸጥታ አካላትን በጋራ በማቀናጀት በሁሉም አካባቢዎች አሰማርቷል ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ ባሻገርም በምርጫው ዋዜማ ፣ በእለቱ እና በድህረ ምርጫ ወቅቶች የተረጋጋና ሰላም የሰፈነበት ለማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤና ተልዕኮ ከመስጠት ባለፈ ከሰፊው ህዝብ ጋር ሰፊ ውይይቶችን በማድረግ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ነው ያሉት ።
በመሆኑም ከየትኛው ጊዜ በበለጠ የተያዙትን ግቦች በሙሉ ለማሳካት አቋም በመያዝ በተለይ የክልል እና የፌደራል የጸጥታው አካላት ፤ የጥፋት ሀይሎቸን ሴራ ለማክሸፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የምርጫው ውጤት በህግ አግባብ በተሰጠው አካል እስኪገለጽ ድረስ ህዝብ ተረጋግቶ እና ለየትኛውም ውዥንብር ጆሮ ሳይሰጥ ድምፁን ማስከበር አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት በሕገ መንግስት የተረጋገጠውን የህዝቦችን ነጻነት እና ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነትን ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እየሰራ ስለመሆኑም አመላክተዋል።
በመሆኑም በተለይ የክልሉ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ በመምረጥ እና ምርጫው ሰላማዊ ፣ ነፃና ፍትሃዊ እንዲሆን ሚናውን እንዲወጣ መጠየቃቸውን ከክልሉ መንግስት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
38
Engagements
Boost Post
36
2 Shares
Like
Comment
Share
Exit mobile version