Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለኬንያውያን የሀዘን መግለጫ አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።

ፕሬዚዳንቷ ለኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ባስተላለፉት መልዕክት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል።

ዳንኤል አራፕ ሞይ ለኬንያ ነፃነት ያደረጉትን ተጋድሎ ያስታወሱት ፕሬዚዳንቷ፥ በኢጋድ ምስረታ ላይ ጉልህ ስፍራ እንደነበራቸውም አንስተዋል።

ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ቢያልፉም ለህዝባቸው እና ለአፍሪካ ደህንነት ባደረጉት በጎ ተግባር ሁሌም ይታወሳሉ ብለዋል በመልዕክታቸው።

ለመላው ኬንያውያን፣ ለኬንያ መንግስት እና ለሟች ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝተዋል።

ዳንኤል አራፕ ሞይ በ95 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን፥ ኬንያም ቀብራቸው እስከሚፈጸምበት ዕለት ድረስ ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጃለች።

መረጃው በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው፤

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version