Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የትምህርት ክፍያ በነባሩ የአስር ወር ክፍያ ሥርዓት መሰረት ይተገበራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ለሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች የዘንድሮ መደበኛው የተማሪዎች ክፍያ በነባሩ የአስር ወር ክፍያ ስርዓትን ተከትሎ እንደሚተገበር ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና፣ ጥራት፣ ሙያ ብቃት፣ ማረጋገጫ ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ እንደገለጹት÷ የ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን መደበኛው የተማሪዎች የትምህርት ክፍያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ1987 ዓ.ም ባወጣው አዋጅ ቁጥር የ206/87 መሰረት በነባሩ የአስር ወር ክፍያ ሥርዓትን ተከትሎ በትምህርት ዓመቱ ሙሉ እንደሚተገበር ተናግረዋል፡፡

እንደ ምክትል ስራ አስኪያጇ ገለፃ÷ ነባሩና ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ ሲተገበር የኖረው የአስር ወር የትምህርት ክፍያ ሥርዓት ለአንድ የትምህርት ዘመን አስር ወር ክፍያ የሚል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በተያዘው 2014 ዓመትም ይህንን የአከፋፈል ሥርዓት ተከትሎ የሚፈፀም ይሆናል ሲሉ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version