Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍጻሜ ውድድር በደማቅ ሥነስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ድምጻዊ አህመድ ሁሴን 1ኛ በመውጣት የ1 ሚሊየን ብር አሸነፊ ሆኗል፡፡
ዝነኛው አቀናባሪ ካሙዙ ካሳ የፋና የክብር እና የዕውቅና ሽልማት አግኝቷል።
በ2013 በ 4 ምዕራፎች ሲካሄድ የነበረው የፋና ላምሮት የባለተሰተጥኦ ድምጻውያን ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል።
ከ6 ሺህ በላይ ድምጻውያን ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ካሉበት በመሆን የድምጽ ናሙና በመላክና በአካል በመገኝት የማጣሪያ ውድድር አካሂደው÷ ያለፉ 36 ድምጻውያን በዓመቱ የውድድር ምዕራፎች ሲፎካከሩ ነበር።
ውድድሩ በየሳምንቱ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭትና በሙሉ የሙዚቃ ባንድ አቅርቦት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
የሙዚቃ ባለሙያ በሆኑ ዳኞችና በተመልካቾች የአጭር የጽሁፍ መልዕክት መቀበያ ድምጽ ዳኝነቱ ተካሂዷል። ከተለያዩ የሞያ ዘርፍ የተውጣጡ ባለሙያዎችም የዳኝነቱ ተሳታፊ ነበሩ።
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው በፍጻሜ ውድድሩ መክፈቻ እንደተናገሩት ÷ ፋና ላምሮት በየጊዜው ከሚያሸልመው ብር በላይ የሚልየን ተመልካቾችን ቀልብና ስሜት ማግኘት ለተወዳዳሪዎች ትልቅ ሽልማትና ትርፍ ነው ብለዋል።
የፋና ላምሮት ዓላማ ባለተሰጥኦችን ለህዝብ አስተዋውቆ መልሶ ለህዝብና ለሀገር የሚሰሩበትን መልካም አጋጣሚ መፍጠር እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
ጥበብ ዘመንን በመዋጀት ድልድይ በማበጀት ሀገርና ህዝብን የማሻገር የጎላ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል፡፡
ለሀገር መሥራትና በሀገር መከበር የላቀ ክብርና ዝና የሚገኝበት ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ÷ ሀገር ያለችበትን ሁኔታ ተረድተው ጥበበኞች ለሀገር እንዲሰሩና በትውልዱና በታሪክ ውስጥ ደምቀው እንዲታዩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በታዋቂው የግጥምና ዜማ ደራሲ የተዘጋጀ “ኢትዮጵያ” የተሰኝ አዲስና ወጥ ሙዚቃ ለመወዳደሪያነት ቀርቦ አራቱም የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች በ3ኛ ዙር ላይ ተወዳድረውበታል።
በአራቱም ዳኞች ድምጽ እና ውሳኔ መሰረት ድምጻዊ ዮናታን ዳመነ የክብር ዋንጫ ሽልማቱን የግሉ አድርጎታል።
በሙዚቃ ቅንብርና በፕሮዲውሰርነት ሥራው ለሀገሩና ለኪነጥበብ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከተው ሙዚቀኛ ካሙዙ ካሳ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የክብር ዋንጫና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።
ድምጻዊ ዮናታን ዳመነ፣ ጌታቸው መስፍንና ሰላማዊት ቦጋለ ከ2ኛ እስከ 4ኛ በመውጣት የደረጃ ዋንጫ እና ለእያንዳንዳቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የ2 መቶ ሺህ ብር ልዩ ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version