አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ከገጠሟት ጊዜያዊ ችግሮች ለማሻገር እጅ ለእጅ ተያይዘን መዝለቅ አለብን ሲሉ በአዲስ አበባ የመስቀል ደመራ ታዳሚዎች ገለፁ።
የመስቀል ደመራ በአል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ፕሬዚዳንት ሳህለወረቅ ዘውዴ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል።
ከእለቱ ታዳሚዎች መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው ዜጎች ኢትዮጵያን አሁን ከገጠማት ጊዜያዊ ችግሮች ለማሻገር እጅ ለእጅ ተያይዘን መቆም አለብን ብለዋል፡፡
ያለህዝብ ተሳትፎ እድገት ስለማይታሰብ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት መሰረታዊ ለውጥ እንዲያመጣና የኢትዮጵያ ሰላም እውን እንዲሆን ሁላችንም ድጋፍና ትብብራችን ሊጠናከር ይገባልም ነው ያሉት፡፡
የበዓሉ ታዳሚዎች ኃይማኖታችን የሚያስተምረን ሰላምና አንድነትን በመሆኑ÷ ለአገራችን ሰላምና አንድነት የበኩላችንን ማበርከት ይገባናል ብለዋል፡፡
አገር ከሌለ ሁሉም ነገር የለምና ሁላችንም ለአገራችን ቅድሚያ እንስጥ ሲሉ ተናግረዋል።
የሃይማኖት አባቶችም ሆኑ ህብረተሰቡ በጋራ ለአገራቸው አንድነት በመቆም የመንግስት ጥረት ያለ ህዝብ ተሳትፎ አይሳካም እና ለኢትዮጵያ ስንል አዲሱን መንግስት ደግፈነው ልንቆም ይገባል ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!