አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተከበረው የደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ለፕሮግራሙ ስኬታማነት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ በሙሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ በፀጥታ አካላት ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
የፀጥታ አካሉ ዕቅድ በማውጣት በርካታ የሰው ኃይሉን በመከላከል ስራ ላይ ማሰማራቱን ፤ ከበዓሉ አስተባባሪዎች ጋር በቅርበት በጋራ በመሰራቱ በመስቀል አደባባይ የተካሄደው የደመራ በዓል ፍፁም ሰለማዊ ሆኖ መከበሩን ፖሊስ ገልጿል ፡፡
በመስቀል አደባባይ የተካሄደውን የደመራ በዓል ተከትሎ በከተማችን በተለያዩ ቤተ-ክርስቲያኖች እና በአንዳንድ ስፍራዎች ደመራ የማብራት ስነ-ስርዓት እንደሚካሄድ የሚታወቅ ነው፡፡
ህብረተሰቡ የፀጥታው ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አመለካካት በመያዝ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት እያበረከተ ላለው ቀና አስተዋፅኦ እንዲሁም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ መላው የፀጥታ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስራ እያበረከተ ያለውን አስተዋፆ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓል የሰላምናየደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!