Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምስራቅ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሰራዊት አባላት የማዕረግ እድገት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሰራዊት አባላት የማዕረግ እድገት መሰጠቱ ተገለፀ፡፡

የዕዙ ዋና አዛዥ ተወካይ ኮ/ል ሲሳይ ታደሰ ÷ ዕዙ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠና ሁሉ ሽብርተኛውን የህወሓት ቡድን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣው በሚገኝበት ጊዜ የእናንተ ኃላፊነት መጨመር ለዕዛችንም ሆነ ለተቋማችን ትልቅ አቅም ይሆናል ማለታቸው ተመላክቷል፡፡

በቀጣይ የሚሰጣችውን ተልዕኮ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በብቃትና በታማኝነት እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version