Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጅማ ከተማ የሠላም ሚኒስቴር ብሔራዊ በጎ ፍቃድ ሰልጣኞች ፅዳት አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ የመስቀል እና የደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሠላም ሚኒስቴር ብሔራዊ በጎ ፍቃድ ሰልጣኞች የከተማ ፅዳት አከናውነዋል።

በጅማ ከተማ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ አስተባባሪነት በተከናወነው የፅዳት ዘመቻ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሁለተኛው ዙር ብሔራዊ የበጎ ፍቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ሰልጣኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

ሰልጣኞቹ መነሻቸውን ከአባጅፋር አደባባይ አድርገው የከተማውን ዋና ዋና መንገዶች ፣ አደባባይ እና የመስቀል ደመራ የሚደመርበትን ስፍራ ስፖርት ማዘውተሪያ (ትንሿ ስቴዲየም) አፅድተዋል።

በፅዳት ዘመቻው ላይ የከተማው ፅዳትና ውበት ሰራተኞችም ተሳታፊ ሆነዋል።

በሰላም ሚኒስቴር የብሔራዊ የበጎ ፍቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ሰልጣኞች አስተባባሪ ወ/ሮ ትዕግስት ኃይለማሪም÷ ሰልጣኞች የአብሮነት እሴትን ለማጎልበት ለማህበረሰቡ አርያነት ያላቸው የተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ እየተሳተፉ መቆየታቸውን አንሰተው፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችና አቅም ደካማ ወገኖችን ገላ ማጠብ ፣ከሰልጣኞች የተሰበሰቡ አልባሳትን ማልበስ እና የመሳሰሉትን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንደሚያከናውኑም ገልጸዋል።

ስልጣኞቹም በጎነትን በብዙ ተምረን ለማህበረሰባችን የምንችለውን ሁሉ እየተገበርን ነው ብለዋል፡፡

በወርቅአፈራው ያለው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version