Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብልፅግና ፓርቲ ሴት አደረጃጀቶች ለጸጥታ ኃይሎች ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ሴት አደረጃጀቶች አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለሚፋለሙ የጸጥታ ኃይሎች ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ እና የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ፣ የአዲስ አበባ እና የክልሎች ሴት አደረጃጀቶችን በማስተባበር ለተፈናቀሉ ወገኖች እና በግንባር አሸባሪውን ህውሓት እየተፋለሙ ለሚገኙ የጸጥታ ሐይሎች ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አስረክበዋል፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት ግንባር ላይ ላሉ የጸጥታ ኃይሎች እና በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከደቡብ ክልል እና ከሲዳማ ክልል ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ እና ሴት አደረጃጀት መሪዎች ባህር ዳር ከተማ እንደተገኙም ነው የተገለጸው፡፡

ዜጎች ወደ ቀያቸዉ ተመልሰዉ የተረጋጋ ኑሯቸዉን እስከሚቀጥሉ ድረስ ድጋፋቸዉን እንደሚቀጥሉ ጦርነቱ የአማራ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ክልሎች የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ጭምር ነዉ በማለት ሁሉም ክልሎች በተባበረ ክንድ በአጭር ጊዜ እንዲቋጭ እና ጁንታዉ እስከወዲያኛዉ እንዲሸኝ አስፈላጊውን እንደሚያደርጉ ስለመናገራቸው ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version