አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእንግሊዝ የተሰራውና የመንገድ ላይ ምልክት ማድረጊያው ሮቦት ሙከራውን አድርጓል።
ሮቦቱ የተለያዩ የመንገድ ምልክቶችን በማስመር ወጪና ጊዜን ይቆጥባል ተብሏል።
የሙከራ ስራውን ባደረገበት ወቅት ውጤታማነት ታይቶበታል የተባለውቅ ሮቦት፥ በአራት ሰዓት በ12 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር መንገድ ላይ ምልክቶችን ማድረጉ ተነግሯል።
ይህ ቴክኖሎጂ ጊዜን በመቆጠብ ስራውን የሚሰሩ ሰራተኞች ያጋጥማቸው የነበረውን ድካም፣ የሚደርሰውን የወገብ ጉዳት እና ምልክት በሚያደርጉበት ወቅት የሚከሰተውን የመኪና አደጋ ይቀንሳል ነው የተባለው።
ይህን ቴክኖሎጂ የተቀበሉት ዋይ ጂ የመንገድ ተቋራጭ ቡድን ሥራ አስኪያጅ ዌን ጆንስተን፥ ቴክኖሎጂው መጨናነቅን ለመቀነስ፣ ጊዜን እና ገንዘብን ለመቆጠብ እንዲሁም ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው ነው ያሉት።
እንዲሁም ለተሻለ እና ጥራት ላለው የመንገድ ላይ ምልክት ያገለግላልም ብለዋል።
ምንጭ፡- traffictechnologytoday.com
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision