አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በ76 ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በኒዮርክ ንግግር አደረጉ፡፡
የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መርሆች የጋራ ተጠቃሚነት እና በሀገራት ሉዐላዊነት ውስጥ ጣልቃ የማይገባ እንደሆነ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
ሀገሬ ከሶስት ዓመት በፊት ለውጥ በማድረግ ለዲሞክራሲ፣ለሰው ልማት፣ ሰብዓዊ መብት እና ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ለተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ፍላጎቶች ላላቸው ቡድኖች የውይይት እና የአንድነት በር እንዲከፈት አድርጋለች ብለዋል፡፡
በዚህም አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል ያሉት አቶ ደመቀ መኮንን ሪፎርሙ ያለፈተና አልተከናወነም ሲሉ ለጉባዔተኛው አብራርተዋል፡፡
በዚህ ሂደት ጥቅሜ ተነካብኝ ያለው ጠቅላይና ወንጀለኛው ቡድን የሀገር መከላከያ ሰራዊታችንን ከጀርባው ካጠቃው እና በርካታ ጥፋት ካጠፋ በኋል መንግስት ህግን ለማስከበር እና ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ እርምጃ ወስዷል፡፡
መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ ሲያደረግ ቡድኑ ድጋፉ እንዲስተጓጎል እና የዜጎች ስቃይ እንዲበረታ አደርጓል፡፡ በውሸት ፕሮፖጋንዳ የተካነው ቡድን በርካታ አፍራሽ ተግባራትን ፍጽሟል፡፡ የውሸት ክስተቶችን አስተጋብቷል፤ቀድሞ በተዘጋጅ ስም የመጣፋት ዝንባሌ ከፍተኛ ዘመቻ አድርጓል፡፡
ህዝባችን ካለበት ችግር አንጻር በቂ ነው ባይባለም መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ መንግስታዊ ግዴታውን ለመወጣት በመስራት እና የተፈጸሙ ወንጀሎች እንዲመረመሩ እንዲሁም እርማጃዎች እንዲወሰዱ አደርጓል ብለዋል አቶ ደመቀ መኮንን፡፡
የጥፋት ቡድኑ በሚከፍላቸው የፕሮፖጋንዳ ሚዲያዎች አማክኝነት እና በተሳሳተ የፖሊሲ አተያይ የውጭ ፖሊሲ መርህ ሲጣስ ተስተውሏል ያሉት አቶ ደመቀ መርሆች መከበርም አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ከወዳጆቻችን የሚመጣውን ገንቢ ምክረ ሀሳብ በመልካም ጎኑ የምንመለከተው ሲሆን፣ አሁን የገጠምን ፈተና ከኢትዮጵያ አቅም በላይ አይደለም፡፡ በጥፋት ቡድኑ ላይ ኢትዮጵያ የጀመረቸውን አርምጃ መደገፍ የቀጠናውን ሰላም መደገፍ ነው ሲሉ አቶ ደመቀ አስምረው ተናግረዋል፡፡
በየትኛውም መልኩ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገባን ሀይል ኢትዮጵያ አትታገሰም ብለዋል አቶ ደመቀ መኮንን፡፡
ኢትዮጵያ ከሁሉም ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት ያላት ሲሆን ከሱዳን ጋር ያላትን የድንበር አለመግባባት በዲፕሎማሲ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ ናት፡፡
የዓባይ ወንዝን የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብት የትውልድ ጥያቄን ምላሽ የያዘ እና ከወንዙ ተጠቃሚ ሀገራት ጋር የጀመርነውን ድርድር መርህን ተከትለን ውይይት የምናደረግ ሲሆን ሁሉንም ተጠቃሚ እንዲያደርግ ጽኑ አቋም አለን ብለዋል አቶ ደመቀ መኮንን፡፡ ነገር ግን የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክታችን በቅኝ ግዛት ሌጋሲ እና ጠቅላይነት አይቆምም ሲሉ አስረግጠዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!