አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግሽን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌያለሁ ሲል ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
መስከረም 21፣ 2014 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የሚከበረው የግሸን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ፖሊስ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ፌዴራል ፖሊስ የሰሜን ፈጥኖ ደራሽ ዳይሬክቶሬት ምክትል ኃላፊ ኮማንደር ምትኩ ዳባ ተናግረዋል።
የአሸባሪው የህዋሃት ቡድን ርዝራዦች ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን በጋር በሰላም እንዳያከብር የሀሰት ፕሮፓጋንዳውን እየነዙ በመሆኑ ህብረተሰቡ ይህ የተለመደ ውሽት ስለሆነ በዚህ ሳይደናገር በዓሉን እዲያከብር ጥሪ አስተላልፈዋል።
አያይዘውም በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ላይ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ጠቅሰው በቀጠናው ላይ የሚገኙ የአትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሰሜን ፈጥኖ ደራሽ ዳይረክቶሬት 4ኛ ዲቪዥን አባላት፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና የከተማው ፓሊስ ጋር በመቀናጀት የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር አካባቢውን በጥምረት እየጠበቁ መሆኑም ገልፀዋል።
ህብረተሰቡ በአካባቢው ፀጉረ ልውጥና ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ህገ-ወጥ ተግባሮች ሲያጋጥመው በፍጥነት አካባቢው ላይ ላሉት የፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ህገ-ወጦችን ለህግ ማቅረብ እንዲቻል ማጋለጥ እንዳለበት ኮመንደር ምትኩ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ምንጭ :- ፌዴራል ፖሊስ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!