Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ውጤታማ የሥራ አፈፃፀም ላላቸው የሠራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ህብረት የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ እና ውጤታማ የሥራ አፈፃፀም ላላቸው የሠራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ፡፡
የዋና መምሪያው ኃላፊ ሜ/ጄ ሀጫሉ ሸለመ ለአባላቱ ማዕረግ ካለበሱ በኋላ ባደረጉት ንግግር ፥ ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ሠራዊቱን የተቀላቀሉትን የሰው ሀይል አያያዝ ፣ የምደባ ቦታ ፣ የመታወቂያ አሰጣጥ ሂደትና የአባላት የሳይኮሜትሪ ምዘና እንዲሁም ሌሎች በርካታ ሥራዎችን ዋና መምሪያው የሚፈጽም በመሆኑ ቀጣይ ብዙ ሥራ ይጠበቃልና ጠንክራችው ሀገር እና ህዝብን እንድታገለግሉ አደራ ተጥሎባችኋል ብለዋል፡፡
ከዕለቱ ተሿሚዎች መካከል ሻ/ል ዶ/ር ሰለሞን አማረ ፣ የማዕረግ ዕድገት በማግኘቴ ደስ ብሎኛል። ለሀገሬና ለህዝቤ ከፍታ ጠንክሬ እሰራለሁ ብለዋል።
ሌሎች ተሿሚዎችም ለማረዕግ ዕድገት በመብቃታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልፀው ፥ ቀጣይ ለሀገር እና ለህዝብ የህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version