Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምሥራቅ ሪጅን በአሸባሪው ትህነግ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳን በወረረበት ወቅት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል።
ኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምሥራቅ ሪጅን በወረዳው ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።
በወረባቦ ወረዳ 09 ጎሀ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት በ 15 ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች 64 ሺህ 428 ደብተሮችን አስረክቧል።
የትምህርት ቁሳቁሱን ለማሟላት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉን የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምሥራቅ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ማስረሻ ገበየ ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በትምህርት ላይ ትኩረት በማድረግ በመላው ኢትዮጵያ በ600 ትምህርት ቤቶች 600 ሺህ ደብተሮችን በማዳረስ ሀገራዊ ኀላፊነትን ለመወጣት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምሯል ብለዋል።
የወረባቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሊድ ሙሐመድ ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች ያደረገው ድጋፍ የተጎጅ ቤተሰቦችን ወጪ የሚቀንስ ነው ብለዋል፡፡ ስለተደረገው ድጋፍም አመስግነዋል።
በተያያዘ የኢትዮ ቴሌኮም የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ሰራተኞች ከ200 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ በሽብር ቡድኑ ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የዱቄት ድጋፍ ማድረጋቸውን አሚኮ ዘግቧል ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share
Exit mobile version