የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እድሳት የተደረገላቸውን ዘጠኝ የአቅመ ደካማ ቤቶችን አስረከቡ

By Meseret Awoke

September 25, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አማካይነት በክረምት የበጎፈቃድ አገልግሎት እድሳት የተደረገላቸውን ዘጠኝ የአቅመ ደካማ ቤቶችን አስረከቡ ።

ዛሬ ማለዳ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በመገኘት በክረምቱ የበጎ ፈቃደኝነት ስራ መኖሪያቸው ለታደሰላቸዉ አረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች ቤቶችን በማስረከብ የአዉደዓመት መዋያ ስጦታዎችንም አበርክተዋል ።

በከተማዋ በቀድሞ ስርዓት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር የተጋለጡ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን መደገፍ የሁላችንም ሀላፊነት በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ከንቲባዋ በርክክቡ ወቅት ተናግረዋል ።

የቤቶቹ እድሳት በፍጥነት ተጠናቀው ለነዋሪዎች እንዲደርሱ ላደረጉ የአዲስ አበባ ውሃናፍሳሽ ባለስልጣን እና የክፍለከተሞች አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ውሃናፍሳሽ ባለስልጣን በዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ ክፍለከተሞች ዘጠኝ የአቅመደካማ ነዋሪዎች ቤቶችን በማደስ እና ሙሉ የቤት ቁሳቁስ በሟሟላት አስረክቧል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!