አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች እና ወጣቶች መስቀል አደባባይን አጸዱ።
የአዲስ አበባ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመቀናጀት የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበትን መስቀል አደባባይን የማጽዳት ስራ ተካሂዷል።
በጽዳት ዘመቻው መርሃግብር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት እና ተወካዮች፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት አድባራት እና ገዳማት አስተባባሪዎች፣ በጎፈቃደኛ ወጣቶች ፣ የፅዳት አምባሳደሮች ፣ ታዋቂ አርቲስቶችና አትሌቶች እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!