አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተመድ 76ኛ ጉባዔ ጎን ለጎን ኢትዮጵያን በተመለከተ ብዥታ ያለባቸውን ወገኖች የማስረዳቱ ሄደት ውጤታማ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከትናት ምሽቱ ፋና 90 ጋር ከኒውዮርክ ባደረጉት ቆይታ ፥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመሩት ልዑክ ከቬኒዝዌላ፣ ጋቦን፣አየርላንድ፣ ኖርወይ፣ዴንማርክና ከኬኒያ መሪዎች ፣ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት እና ከሴራሊዮን ውጭጉዳይ ሚንስትር ጋር ተወያይቷል ብለዋል።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራ እና በአፋር ክልሎች ስለፈጸመው ጥፋት ፣ መንግስት እርዳታን ለማድረስ እያደረገ ስላለው ጥረት ፤እንዲሁም ከነዚህ ሀገራት ጋር ተባብሮ ስለመስራት ያለውን ፍላጎት ገልጸውላቸዋል።
ልዑኩ ከሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ሀላፊዎች ጋርም ተወያይቷል።
የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ለማድረግ ያሉ ተግዳሮቶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን አንዳንድ ወገኖች በኢትዩጵያ በኩል የሚደረገውን ጥረት ያልተገነዘቡ መሆኑን አንስተው ውይይቱ እንዲገነዘቡ አድርጓቸዋል ብለዋል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ።
ከሰኞ ጀምሮ የቀጠሉ ውይይቶች በአጠቃላይ ውጤታማ ነበሩ ሲሉ አምባሳደሩ የተናገሩት።
ሀገራቱ ድጋፋቸውን ከፍ ለማድረግ ፍላጎት አሳይተዋል ፤በተለይ የውጭ ጉዳይ ባለስልጣናት ጋር በተደረገ ውይይት።
ኢትዮጵያ የጀመረቺውን አፍሪካዊ መፍትሄ አጠናክራ እንድትቀጥል ጥሩ ውይይት ተደርጓል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!