Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጎግል የደንበኞችን የግል ተንቀሳቃሽ ምስል በስህተት ለሌሎች በማጋራቱ ይቅርታ ጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ጎግል የተወሰኑ ደንበኞችን የግል ተንቀሳቃሽ ምስል  በስህተት ለሌሎች በማጋራቱ ይቅርታ ጠይቋል።

ችግሩ ደንበኞች የግል ገፃቸውን ለመለየት የሚስችለውን ምስል  ለመጫን በሚያስችለው ክፍል ላይ የተፈጠረ መሆኑ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል።

ስህተቱ ለአራት ቀናት ማለትም ካሳለፍነው ጥቅምት 21 እስከ 25 ቀን  2019 ድርስ የቆየ መሆኑ ነው የተገለጸው።

በዚህ ወቅትም በችግሩ የተጠቁ ደንበኞች የራሳቸው ያልሆነ አሊያም ተገቢውን ጥራት ያላሟላ ተንቀሳቃሽ ምስል የደረሳቸው መሆኑ ተጠቁሟል።

ይሁን እንጂ ኩባንያው ችግሩ በምን ያህል ደንበኞቹ ላይ ተከስቶ እንደነበር ከመግለፅ ተቆጥቧልል።

አሁን ላይ ችግሩ መስተካከሉን የገለጹት የኩባንያው ቃል አቀባይ፥ለተፈጠረው ስህተት ደንበኞችን ይቅታ ጠይቀዋል።

በቀጣይ መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥልቅ  ምርመራዎችን በማካሄድ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅ የሚደረግ መሆኑ ተጠቁሟል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

 

Exit mobile version