Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሰሚ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከዩክሬኑ ሰሚ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት በተካሄደው ሰምምነት መሰረት ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመሳሰሉባቸው ጉዳዮች በርካታ መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን በስፋት ተባብረው መስራት በሚችሉባቸው መስኮች ላይ አተኩረው ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸው ተጠቅሷል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ እንደሚያመለክተው÷ ዩኒቨርሲቲዎቹ በምርምር፣ የአጭርና የረዥም ጊዜ ስልጠናዎች፣ በሠራተኛና ተማሪዎች ልውውጥ፣ በዓለም አቀፍ የጋራ አጀንዳዎችና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና እና የሰሚ ስቴት ዩኒቨርሲቲን በመወከል ዶ/ር ቴትያና ሜይቦሮዳ የዩኒቨርሲቲው የውጭ ግንኙነት እና ትብብር ተባባሪ ዳይሬክተር ፈርመዋል፡፡

ስምምነቱ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ እየታየ የሚታደስ መሆኑን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version