Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት 12 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰዎች ለሰዎች ድርጅት 12 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ከ14 አይነት በላይ ድጋፎች ማድረጉን የድርጅቱ ሀገር አቀፍ ተጠሪ ይልማ ታየ ገለጹ፡፡
ድጋፎቹ በወሎ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተበረከቱ ሲሆን÷ አልባሳት የምግብ እህል ና የንጽህና መጠበቂያዎችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
አሁን የተደረገው በቂ አለመሆኑን ጠቅሰው ወደፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡
እኛ እያለን ወገን አይራብም ያሉት ሻለቃ አትሌት ሀይሌ÷ አሁንም ድጋፎች ይቀጥላሉ ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ ለተደረገው ድጋፍ አመሰግንዋል።
በከድር መሀመድ እና ሀብታሙ ተክለስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version