አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሰብልና የእንስሳት መኖ የማስፋፋት ሥራ በአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳ ላይ እየሰራ ነው።
በዚህም የጐርፍ ውሃን በማቀብ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለአካባቢው አዲስ የሆነውን እንቁ ዳጉሳን ጨምሮ በማሽላ፣ ጤፍ፣ በቆሎና ሌሎች ሰብሎች ላይ ነው የማስፋፋት ስራ እየተከናወነ ያለው፡፡
ዩኒቨርሲቲው 20 ነጥብ 9 ሄክታር መሬት ላይ በሙከራ ደረጃ በጭፍራ ወረዳ አርብቶና ከፊል አርሶ አደሮች ማሳ ላይ የተሻሻሉ ዘሮችን ያቀረበ ሲሆን ፥የግብአት አቅርቦትና ሙያዊ ድጋፍም አድርጓል፡፡
የዩኒበርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ፋሪስ ኃይሉ፥ የምርምርና የማማስፋቱ ስራ ዝናብና እርጥበት አጠር በሆነው አካባቢ ምርታማነትን ከፍ በሚያደርጉ ሰብሎች ላይ በማተኮር እንደሚሰራበት ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዉ የማሳ ላይ ጉብኝቱን አርሶ አደሮች ባለሙያዎችና አመራሮች በተገኙበት አካሂዷል፡፡
በአንድነት ናሁሰናይ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
49
Engagements
Boost Post
47
1 Comment
1 Share
Like
Comment
Share