አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከኖርዌይ እና ዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል።
አቶ ደመቀ ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪ ኤሪክሰን ሱሬይድ በኒውዮርክ የስራ ቆይታቸው ተገናኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዴኒማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ ጋር ተገናኝተው በልማት ትብብር እና በሰብዓዊ አገልግሎት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!