አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ለአገር መከላከያ ሰራዊት “ደጀንነታችንን ለማሳየት ድጋፉን አድርገናል” በማለት የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ዳይሬክተር አቶ የሰውዘር በላይነህ ተናግረዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ እየተፋለመ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነት ለማሳየት ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የበሬ ሰንጋዎች ግንባር ድረስ በመሄድ ዛሬ አበርክቷል።
በሚኒስቴሩ የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ዳይሬክተር አቶ የሰውዘር በላይነህ “ለአገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነታችንን ለማሳየት ድጋፉን አድርገናል” ብለዋል።
በቀጣይም ለሰራዊቱ የሚያደርጉትን የደጀንነት ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በወሎ ግንባር የኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ ተወካይ ሰራዊቱ አሸባሪውን ኃይል በአጭር ጊዜ ለማጥፋት ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ለሰራዊቱ ያሳየውን ደጀንነት በማመስገን÷ “ድጋፉ ለሰራዊቱ ከፍተኛ የሞራል ስንቅ በመሆን ጠላትን በአጭር ጊዜ ለማጥፋት ያግዘዋል” ብለዋል።
በወሎ ግንባር ጠላትን ለመደምሰስ አኩሪ ጀብድ እየፈጸመ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊት የተደረገው ድጋፍ ድሉን ለማፋጠን ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!