አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው ሃገራዊ ምርጫ ድጋሚ እንዲካሄድባቸው የተወሰነባቸው የምርጫ ክልሎችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም ባስኬቶ ልዩ – ለክልል ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፣ቡሌ – ለክልል ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ጉመር 2 – የክልል ምክር ቤት መስቃና ማረቆ – ለክልል ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡