አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም በሚካሄደው ጉባኤ አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት እንደሚመሰረት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ገለጹ።
አፈ ጉባኤዋ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 15 ፣2014 5ኛው ዙር የጨፌ ኦሮሚያ ማጠቃለያ እና 6ኛው ዙር ጨፌ ኦሮሚያ የመጀመሪያ ጉባኤ ይካሄዳል ብለዋል።
በጉባኤው ነባር የጨፌው አባላት የሚሸኙበትና አዲሶቹ የሚተኩበት እንደሚሆንም አስታውቀዋል፡፡
በጉባኤው አዲሱ የክልሉ ርእሰ መስተዳድርን ጨምሮ አዲስ የካቢኔ አባላት እንደሚሰየሙ ወ/ሮ ሎሚ በዶ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
በቀጣይ 5 አመታት የኦሮሚያ ክልልን የሚመራው አዲስ የክልሉ መንግስት ምስረታው ከመካሄዱ በፊት የጨፌ ኦሮሚያ 2013 ላይ ያልቋጫቸውን እየተጠናቀቁ ያሉ ረቂቅ አዋጆችና አንዳንድ ጉዳዮች እየታዩ መሆኑን የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!